PILGRIMAGE TOURS
ኢየሩሳሌም እግዚያብሔር ወልድ በስጋ ተገልጦ ታላላቅ ታምራት የሰራባት ክቡር ስጋውን ቆርሶ ክቡር ደሙን አፍስሶ ለሰው ልጆች ያለውን ፍቅር የገለጸባት ቅድስት የሰላም ከተማ ስትሆን ኢየሩሳሌምን መጎብኘትና ከበረከቱ መሳተፍ የነፍስ እርካታን ያስገኛል ፡፡

በመሆኑም የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች በሆኑት ኢትዬጵያውያን ዘንድ ልዩ አድናቆትና አክብሮት የሚሰጣቸው ቅዱሳን ካናትን ጨምሮ የጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን በዓለ ልደትና በዓለ ትንሳኤ በኢየሩሳሌም ለማክበር ለሚፈልጉ ምእመናን ዱካ አስጎብኚና የጉዞ ወኪል ምዝገባ መጀመሩን በአክብሮት ይገልጻል፡፡

በመንፈሳዊው የኢየሩሳሌም ጉዞ የሚጎበኙ ቅድሳት መካናት ፡-

 • ጌታችን የተወለደበት ቤተልሄም
 • እረኞች የነበሩበት ዋሻ
 • ከጲላጦስ አደባባይ እሰከ ቀራኒዮ ጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ- የተጓዘበት ፍኖተ መስቀል እንዲሁም የተቀበረበት ጎልጎታ
 • እመቤታችን የጸለየችበት ስፍራ
 • ንግስት እሌኒ መስቀሉን ያስወጣችበት ቦታ
 • በቤተ ሳይዳ መጻጉዕ የተፈወሰበት ውሃ /ኮሬ/
 • ምስጢረ ቁርባን የተፈጸመበት አዳራሽ
 • በንጉስ ሰለሞን የታነጸው የመጀመሪያው ቤተ መቅደስ
 • በኢየሩሳሌም በስተምስራቅ ትይዩ ያለውና የቄጵሮን ሸለቆ ተሻግሮ የሚገኘው የደብረዘይት ተራራ
 • ጌታችን ስለ ኢየሩሳሌም ያዘነበት ቦታ
 • ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን ከባረካቸው በኋላ በዓይናቸው እያዩት ያረገበት ቅዱስ ቦታ ኢያሪኮ
 • የጨረቃ ከተማ እየተባለ በሚጠራው ኢያሪኮ አካባቢ የሚገኙ ገዳመ ቆርንቶስ # የኤልሳ ምንጭ # የዘኬዎስ ሾላ # የዮርዳኖስ ወንዝ #የኢትዮጵያ ገዳም # የታቦር ተራራ# የገሊላ ባህር# ቃና ዘገሊላ # ናዝሬትና የመሳሰሉት መንፈሳዊ ቅዱሳን መካናት ይጎበኛሉ፡፡

Socialize with us on